በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ለዓለም ዓለም አሜን።
ቀስተደበና፥ ዓላማችሁ ምንድ ነው?
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ ዓላማችን በአጠቃላይ በኤርትራ በተለይ ደግሞ በአሥመራ ከተማ ሃይማኖታችን ተዋህዶ ነን የሚሉ በግብራቸው ደግሞ ተዋህዶ ያልሆኑ ቁጥራቸው እየበዛ በመምጣቱ ከምንም በላይ ደግሞ በ20 የሚደርሱ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ስላበቡ ህዝብንም ማሳሳት ስለጀመሩ አማኙ የተወህዶ ህዝብ በሃይማኖት ሊኖረው የሚገባ እውቀት ለማሳደግ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ዲያቆናት ማፍራት ነው። በሁሉም አብያተ ክርስትያናት ተዋህዶ እምነት ማስፋፋት ደግሞ የረጅም ጊዜ ዕቅዳችን ነው።
ጥያቄው፥ 1ኛ. ሥርዓተ ቤተ-ክርስትያን አሥመራ በአሁን ሰዓት በሀገራችን ኢትዮጵያ በአግባቡ ሥራ ላይ ባይውልም አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለውን ቃል አዋዲ መሆኑ ይታወቃል እንዲህ ከሆነ ታድያ የሰንበት ት/ቤት ሥልጣን እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውን ጥያቄ መነሳቱ ሁላችንን የሚጠቅም ጥያቄ ነው። (የሰንበት ት/ቤት ክፍል ሥራና ኃላፊነት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።)
2ኛ. ካህናትን የማፍራትም ሆነ የመልመል ድርሻ የማን ነው? የሰንበት ት/ቤት ድርሻ ነው ብለው ያምናሉ?
3ኛ. አንዲት አጥቢያ ቤ/ያን ሰንበት ት/ቤት ከሌላይኛይቱ አጥቢያ ሰንቤት ት/ቤት መልካም ወዳጅነትና መንፈሳዊ መቀባበል ውጪ ይህ ትክክል ነው ይህ ትክክል አይደለም የሚል ጣልቃ ገብነትስ ከየት የተገኘ ሥልጣን ነው? ለመሆኑ ይህ ህገ ወጥ ድርጊት የሚያበረታት ሥርዓተ ቤተ-ክርስትያን ይኖር ይሆን?
ቀስተደበና፥ ሰንበት ት/ቤት ከቤተ-ክርስትያን ጋር ያለው ዝምድና ምንድ ነው? በተለይ የእናንተ?
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ እኛ በኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ሥር ነው የምንተዳደረው። ሰበካ ጉባኤው ልጆቻችን ናችሁ ብሎ አምኖን እኛ ደግሞ በበኩላችን አባቶቻችን ብለን አምነንላቸው በመጠኑ ከሥራቸው ተጠለልን። ግኑኝነታችንም በመንበረ ፓትሪያሪክ ደረጃ እውቅና አለን። ኮፒውንም ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ጋር አለ።
ቀስተደበና፥ መርጌታ ክንፈ ርግበ ማርቆስ የተባሉ መሪ (ሃላፊ) ይህ በቤተ-ክርስትያን ላይ የተፈጸመ መንስኤ ናቸው ይባላሉ ከእናንተ ጋር ምን ግኑኝነት አላቸው?
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ ሰብሳቢያችን ናቸው። መምህራች ናቸው። ችሎታቸው ያረጋገጡ ባለሞያ ስለሆኑ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሁሉም ኦርተዶክስ አማኝ ዘንድ ታምኝና ታዋቂ ስለሆኑ መሪያችን ናቸው። እሳቸው የመዝገበ ቅዳሴ ና የትርጓሜ መጻህፍት መምህር ናቸው። ያስመሰከሩ አባት ናቸው።
ጥያቄው፥ 1ኛ. ውድ አንባቢ! ከአንድ ሃይማኖታችንን ጠብቀን እናስጠብቃለን ከሚሉ አካላት ምን ይጠብቃሉ? ልማት ወይስ ጥፋት? “ተዋህዶ” እምነታችን እንጠብቃለን ብለው የተነሱ የተቆርቋሪዎቹ መሪና አባትስ በየተኛው መልካቸውና ማንነታቸው በአደባባይ ተገለጡ? በአልሚነታቸው ወይስ በአጥፊነታቸው? ሌላው ይቅር ዲያቆኑ የአባታቸው ሥራም ሆነ እሱን መሳዮች ድርሻ አልካደም በምትኩ “ሰብሳቢያችን ናቸው። መምህራች ናቸው።” ብሎ ኮራባቸው እንጂ።
2ኛ. እስከ አሁን የዚህ እኩይ ምግባር ዋና ተዋናይ የሰይጣኑ ማኅበር “ማኅበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ የምትጠራጠሩ ወገኖች ዲያቆኑ መምህራቸውና መሪያቸው ሲናገር ሲገልጻቸው በሌላ መልኩ የወጠጤ ስብስብ ከሚል ትችት ለማምለጥ “ከሁሉም በላይ ደግሞ በሁሉም ኦርቶዶክስ አማኝ ዘንድ ታምኝና ታዋቂ ስለሆኑ መሪያችን ናቸው። እሳቸው የመዝገበ ቅዳሴና የትርጓሜ መጻህፍት መምህር ናቸው። ያስመሰከሩ አባት ናቸው።” በማለት በምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ሞያዎችና አባቶችን ከፊት ለፊት እያስቀደምክ ሰይጣናዊ ሥራ መፈጸምስ የማን ስልት ናት? “ማኅበረ ቅዱሳን” ካልሆነ በስተቀረ!።
ቀስተደበና፥ በእናንተ እና በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች ያለውን አለመግባት ምንድነው? (መነሻው ምንድን ነው?)
ዲያቆን መርሀ ክርስቶስ፥ ሁሉ እንደሚያውቀው ቤተ-ክርስትያኒቱ የኦርቶዶክስ (ተዋህዶ) እምነት አማኞች ናት። ስለሆነም እነዚህ የተመሰረቱ ሰንበት ት/ቤቶች ሌላ ዓላማ ስላላቸው ነው ምክንያታችን።
ጥያቄው፥ 1ኛ. “ሌላ ዓላማ ስላላቸው” በመሰረቱ ስተዋል ተብለው እየተወቀሱ ያሉ ከቤተ-ክርስትያኒትዋ ስር የሚተዳደሩ ሰንበት ት/ቤቶች ዓላማ የማንን ተልዕኮ ማዕከል አድርገው እንዲንቀሳቀሱ ነው የሚጠበቀው? የቤተ-ክርስትያኒትዋ ወይስ እነዚ ግለሰቦች (ማኅበራት) ዓላማ ማዕከል ያደረገ?
2ኛ. ስተው የተገኙ እንደሆነም ስታቸዋል የማለት ሥልጣን ያለው ማን ነው? “እኛ በኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ሥር ነው የምንተዳደረው።” እንዲል በመላ ምድረ ኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መዋቅሩን ዘርግቶ መንቀሳቀሱ ምን ይባላል? እንዲህ ከሆነ በአሥመራ ከተማ የሚገኘው ገባሬ እኩይ ዋና ቢሮው አዲስ አበባ ያደረገ “ማኅበረ ቅዱሳን” ንኡስ ማዕከል ሳይሆን ራስ ነው ያስብለናል።
ቀስተደበና፥ እሺ እነዚህን ምን ነው ልታደርጓቸው የምትፈልጉ?
ዲያቆን መርሀ ክርስቶስ፥ ከቤተ-ክርስትያናችን አከባቢ እንዲርቁልን እንዲወጡልን ነው የምንፈልገው።
ጥያቄው፥ ጭራሽ ቤተ-ክርስትያኒትዋ ሰው የላትም ወይ! አላሉም ውድ አንባቢ ሆይ? ንፍጡ ያልጠረገ ምራቁ ያልዋጠ ሁላ በቤተ-ክርስትያን ዓውደ ምህረት ላይ እንዳሻው ሲሆን? ውድ አንባቢ ሆይ በኢትዮጵያ ምድር “ማኅበረ ቅዱሳን” ተብሎ የሚታወቀው የርኩሳን ስብስብ በየትኛው ምዕርፍ ነው የሚያውቁት? በወንጌል ሰባኪነቱ ነው ወይስ በሳዳጅነቱ?
ቀስተደበና፥ ከዚህ በፊት የተባረሩ አሉ?
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ አዎ! ከዚህ በፊት በባረንቱ፣ ባጽዕ፣ ዓዲ ቀይሕ፣ ደቀምሓረ፣ መንደፈራ፣ ዓዲ ኳላ፣ ሓጋዝ፣ ናቕፋ፣ ነፋሲት፣ ጊንዳዕ፣ ነበሩ በህዝቡ ተባረዋል። በአንዳንድ ከተሞች በእውነትኞች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተተክተዋል። በተቀሩትም ቀስ በቀስ ይተካሉ።
ቀስተደበና፥ ከገለጻችሁት በቀር በዋናነት የሚያጣላችሁ ምንድ ነው ብለን መናገር እንችላለን?
ዲያቆን መርሀ ክርስቶስ፥ በዋናነት የሚያጣላን ኦርቶዶክስ አለመሆናቸው ብቻ ነው። ለምሳሌ ያህል መካነ ህይወት መድኃኔዓለም (የኦርቶዶክስ ቤ/ያን ነው) እስከ 45 ነጥብ የያዘ መረጃ አለን። ምን እንደሚሉና ምን እንደሚያስተምሩ…።
ቀስተደበና፥ እሺ ምንድ ነው የሚሉ?
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ ከኦርተዶክስ እምነት ውጪ የሆነ ትምህርት ያስተላልፋሉ። በጋዜጣና በመጽሔት የተሳሳቱ ምረጃዎች አሉ እየው ይህን ጋዜጣ …
ጥያቄው፣ በይፋ የወጣ የስህተት ትምህርት ካለ ለዛውም ማንነታቸውና አድራሻቸው ከማይታወቁ ሳይሆን “መካነ ህይወት መድኃኔዓለም ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ሰንበት ት/ቤት የቤተ-ክርስትያኒትዋ መሪዎችና አባቶች ሳያውቁት ቀርተው ነው ማኅበር ተነስቶ የሚያወግዝ? ወይስ የቤተ-ክርስትያን መሪዎች አባቶች ጭምር ጸረ-ተዋህዶ እምነት ናቸው ነው መልዕክቱ?
ቀስተደበና፥ ከኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ውጪ የሚገኙት ሌሎች ለምሳሌ ከእነ “መሉ ወንጌል” ግኑኝነት አላቸው?
ዲያቆን መርሀ ክርስቶስ፥ እንዴታ! ከእነሱ ጋር ግኑኝነት እንዳላቸው መረጋገጫ አለን። እዚህ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን እምነት ተከታዮች ይመስላሉ ሲወጡ ደግሞ ሌላ ነው የሚመስሉ። እነዚህ የማርያም እና የሥላሴ ቤ/ያን ሰንበት ት/ቤት ወደ ሙሉ ወንጌል እየሄዱ ነው የሚሰብኩ። መንበረ ፓትሪያሪክ ያውቃል።
ጥያቄው፥ ይሁን መረጃም ይኑር እንበል መረጃው መቅረብ ያለበት ለማን ነው? ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ጥፈተኛ ነህ ተብሎ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት ያለበትስ በማን በኩል ነው? ሥልጣኑ ያለው ማን ነው? ከአንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሥር ነው የምንተዳደርው በሚሉ ጎበዞች ወይስ በቤተ-ክርስትያኒትዋ የሚመለከታቸው አካላት? ሌላው ይቅር በአመጻ ከመስከራቸው የተነሳ ወጣቶቹናን የሰንበት ት/ቤቶች ሥም ማጥፋት አልበቃ ብሎአቸው የመንበረ ፓትሪያሪክ ቢሮና አባቶችን ለመወንጀል ወደኃላ አለማለታቸው ነው።
ቀስተደበና፥ የሚታወቅ ከሆነ ለምን በቤተ-ክርስትያን ውስጥ እንዲቀመጡ ፈቀደላቸው? (ዲያቆኑ ከፍ ብሎ መናፍቅነታቸው “በመንበረ ፓትሪያሪክ ያውቃል” ሲል ለሰጠው ምላሽ ያቀረበለት ጥያቄ ነው።)
ዲያቆን መርሀ ክርስቶስ፥ አንዳንድ በመንበረ ፓትሪያሪክ ከፍተኛ ሥልጣን ይዘው የሚገኙ በመካነ ህይወት እና በፍኖተ ብርሃን በዋና ኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች ስለሚገኙ ነው።
ቀስተደበና፥ ይህ አለ መግባባት (መበጣበጥ) የሚቀጥል ይመስልኃል?
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ አዎ! ቤተ-ክህነት ካልጠራ የሚያቆም አይመስለኝም። እናቶቻችን ተያይዘውታል። ረገብ ያለው ለጊዜ ነው እንጂ ቤተ-ክርስቲያን ብትጠራም ቤተ-ክህነት እስካልጠራ ድረስ የሚያቆም አይመስለኝም።
ቀስተደበና፥ እናንተ ከኢትዮጵያ የተባረራችሁ ናችሁ? በምንድነው በዚህ የምትታሙ?
ዲያቆን መርሀ ክርስቶስ፥ 300 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አለን በአንድ ወቅት ኢትዮጵያውያን ናቸው ብለው አሳሳረውናል
ዲያቆን ኣኽሊለማር፥ “... ኃይማኖት ዜግነት ይለያል እንዴ? ድንበር አለው እንዴ? እምነትና ፖለቲካ በተናጠል መታየት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል”
ቁም ነገሩ! የሰይጣን ብልጠቱ እሳት ለኩሶ ዘውር ማለቱ አይደል የሚባለው ደግሞስ ከመቼ ጊዜ ጀምሮ ነው ሌባና ገዳይ ሰርቄአለሁ ገድያለሁ ብሎ የሚያቀው? ዋናው ጋዜጠኛ (የቀስተደበና) ይህን ጥያቄ ለምን ሊያነሳ ቻለ? ወደ ማለት ብንመጣ ሐቁ ኩልል ብሎ መውጣቱ ነው። ጋዜጠኛው ጥያቄው ሊያነሳበት ከቻለባቸው ተጨባጭ ምክንያቶች መካከል፥
1. ጠያቂው አካል (ጋዜጠኛው ማለት ነው) ህውከቱን እና ብጥብጡን አስመልክቶ እስከ ጠየቀ ድረስ “እናንተ ከኢትዮጵያ የተባረራችሁ ናችሁ?” ሲል ያነሳው ጥያቄ ከዚህ በፊት በሃይማኖት ሽፋን የተከሰቱ ህውከቶች እንዳሉና በሚመለክታቸው አካላት በተደረገ የማጣራት ምርመራም የእንዲህ ዓይነቱ ህውከቶች ቆስቋሾች እነዚህ “ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንጠብቃለን” ብለው የተነሱ በማኅበሩ መርዝ ክፉኛ የተለከፉ ከኢትዮጵያ ወደ ሀገራቸው በተመለሱ ተልደ ኤርትራውያን ግለ ሰቦች የሚመራና የእነሱ ቁጥር ብዛት ያለው አጥፊ ቡድን ለመሆኑ ተጨባጭ መረጃ እንዳለ በማንም ዘንድ ስለሚታወቅ ነው።
2. ይህ ጥያቄ የለም! በማለት እውነቱን ለማድበስበስ ብንሞክር እንኳን ጥያቄው በሌላ መልኩ ማየት ይቻላል። ይኸውም ይህ ቡድን ባይሆንም ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ኤርትራውያን ሆኖው ሆነም ግን በኢትዮጵያ በነበሩበት ዘመን በሃይማኖት ሥም ሌላ ፖለቲካ የሚያራምድ ገዳይ ማኅበር “ማኅበረ ቅዱሳን” የከተተባቸው የግርግር አባዜ ሳይለቃቸው ቀርቶ ይህን እኩይ ምግባር ዛሬም እየፈጸሙና የሚፈጽሙ እንዳሉ ነው የሚያመላክተው “እናንተ… ናችሁ? እንዲል
3. በኢትዮጵያ ውስጥ በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ድርጅት (“ማኅበረ-ቅዱሳን”) በኤርትራ ምድር በዚህ ሥም መንቀሳቀስ ባለመቻሉና በውስተ ታዋቂነት ግን የተበላ በመሆኑ ጋዜጠኛው አሳምሮ ስለሚያውቅ እና ማኅበሩ በዚህ አጥፍቶ በመጥፋት ረገድ ላይ ጎልቶ ስለሚታወቅም ነው።
4. ማኅበሩ (“ማኅበረ-ቅዱሳን”) በሀገራች (በኢትዮጵያ) የኃይማኖት ካባ ለብሶ በኢ/ኦ/ተ/አብያተ-ክርስትያናት ምእመናን ተከታዮችዋም ሆነ በመሪዎችዋ መካከል የለኮሰው እሳትና ትርምስ የአደባባይ ሚስጢር በመሆኑና በኤርትራ ምድር እየተከሰተ የምጣውን እንግዳ ድርጊት በተመሳሳይ ስልትና ዘዴ መፈጸሙ።
5. ቀለል ስናደርገውም ኋላ ኋላ ነውጠኞቹና ሁከት ፈጣሪዎቹ (የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ጠባቂዎች ነን ባዮች) ወጣቶች አባላት በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው “በድንበር” በውዝግቡ ምክንያት ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የገቡ ኤርትራውያን በመሆናቸው።
6. የሆነውና ገና ይቀጥላል የተባለለት የህዝብ ደህንነትንና የሀገርን ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል ሁከት ከዚህ ቀደም በመንፈሳውያን ዘንድ ይህን ያህል የከፋና ገፍቶ የወጣ የእርስ በርስ ግጭት ጸብና መለያየት ታይቶ አለምታወቁና ሌሎች በርከት ያሉ ጭብጥ ያላቸው ተጠቃሽ ምክንያቶች ግምት ውስጥ በማስገባት ነበር የቀስተደበና ጋዜጠኛ “እናንተ ከኢትዮጵያ የተባረራችሁ ናችሁ? በምንድነው በዚህ የምትታሙ?” አንድም ይህ እኩይ ተግባር ኤርትራ በቀል አለመሆኑ ለማሳየት ሲል ጥያቄውን በእውቀት የሰነዘረ።
እንግዲህ ለዚህ ለተነሳ ጥያቄ መልስ ሰጪዎች አዎ! ነን የማኅበረ-ቅዱሳን “መንፈሳዊ” ሽብር ነዢ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚዎች ነን! የሚል ፍጥጥ ያለ መልስ ይሰጡናል በማለት ልቡን ጥሎ የሚጠብቅ ባለ አእምሮ ያለ አይመስለኝም። የአብርሃም በግ ካልሆነ በስተቀረ። ያም ሆነ ይህ ግን መልስ ሰጪዎቹ “ዲያቆናትም” እንደሆኑ አዎ! ነን በማለታቸው በገለልተኛ ዜጎች የትም በሌሉ (በሃይማኖት በኩል ለማለት ተፈልጎ ነው) ኤርትራውያን ዘንድ ሊደርስባቸው የሚችል ጫናም ሆነ ሊመቱት ከሚያስቡት ግብ የሚጨናግፋቸው በመሆኑ ምንም “ሃይማኖተኞች” ቢሆኑም ጥያቄውን የውሸት ቃላቸውን በመስጠል አልፈውታል።
ውድ አንባቢ ሆይ! ቀደም ብሎ በክፍል አንድ አሁን ደግሞ በክፍል ሁለት ገናም በሚቀጥል በተጨባጭ መረጃዎች የታጀበ ከ10 ዓመታት በፊት በኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የተከሰተውን አለመግባባትና የተለኮሰው የመለያየትና የመበጣበጥ እሳት አሁንም በተቀናጀ መልኩ እየቀጠለ ያለው የሰይጣኑ “ማኅበር-ቅዱሳን” ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ለመሆኑ ተጨማሪ መረጃ የሚጠይቅ ቅን ሰው ወይንም ደግሞ የተጻፈውን በትክክል አንብቦ የመረዳት ችሎታ ያለው ሰው ያለ አይመስለኝም ይቅር የዚህ ሁሉ ጥፋትና ሁከት ሙሉ ኃላፊነት የሚወሰደው “ማኅበረ-ቅዱሳን” ለመሆኑ ሊጠራጠር።
የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችንና ቤተ-ክርስቲያናችን ይጠብቅ!
ጥበብ በዚህ አለ!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
ካብ ውሽጢ ኤርትራ ዝተረኽበ ንቤተ ክርስቲያን ተዋህዶ ንምቁጽጻር ብመንግስቲ ኤርትራ ክካየድ ዝጸንሐን ዘሎን ሽርሒ ዘቃልዕ ቪድዮ
ድኳን መጻሕፍቲ/Book Store
ራድዮ ቃለ ኣዋዲ