S5 MP3 Player - плагин joomla Mp3

ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብራኤል እተባህለ ኢትዮጵያዊ፥ ብዛዕባ ኣመሥራርታን ኣመዓባብላን ማሕበረ ቅዱሳን ዝበሃል ማሕበር ኣብ ኢትዮጵያ ዝመሠረቱ፥ ናብ ኤርትራ መሓውሩ ከመይ ገይሩ ከም ዝዘርግሐ፥ ዝገልጽ ብኣምሓርኛ ዘውጽኦ ጽሑፍ፥ ዝረኸብናዮ ከም ዘለዎ ነቕርቦ ኣሎና፡ብተወሳኺ፥ ዲያቆን ሙሉጌታ: ሠለስተ ተኸታተልቲ መጻሕፍቲማሕበረ ቅዱሳን ወይስ ማሕበረ ሰይጣን?” ዝብል ዝጸሓፎ መጻሕፍቲ ኣምላኽ እንተ ፈቒድዎ ብትግርኛ ተርጒምና ክንዝርግሖ ከነቅርቦ ኢና። ንሕጂ ግን ብቐጥታ ምስ ቤተ ክርስቲያንና ዝተተሓሓዘ ጽሑፍ ስለ ዝኾነ ከም ዘለዎ ቋንቋኡውን ከይቀየርና ናብ ተኸታተልትና ንቕርቦ።

የ ማኅበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊና ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት! ክፍል-1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ለዓለም ዓለም አሜን።

ሰው ከሰው እይታና ግዛት ሊያመልጥ ይችላል ምንም ጥያቄ የለው! የሚያየኝ፣ የሚሰማኝ የለም በማለትም ያሻውን ይሆናል ያደርጋልም ለዚህም ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም። ምስክር በሌለበት ሰው ገድሎም በህግ ፊት ነጻ ነኝ ብሎ ሞግቶ ያመልጣል፤ እንደው ተጓጉያለሁ በማለት ቅሬታውን አሰምቶ ኪሳራውን ይጠይቃል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እግዚአብሔር የለም! ማለት አይደለም።እነሆ አህዛብ (በፊትህ) በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸውተብሎ እንደተጻፈ ሰው ከሰው እይታ ሊያመልጥ ስለቻለ ከእግዚአብሔር ዕውቀትና እይታም ያመልጣል ሊያመልጥም ይችላል ማለት ግን አይደለም። በቃላት ለመግለጽ መመኮሬ በራሱ የመልዕክቴን ክብደት ያቀልብኛል እንጂ እንደ እሳት ነበልባል የሚንቦለበል ከእግዚአብሔር ዓይን ሊያመልጥ የሚቻለው ፍጡር ከቶ የለም!! 

ኣብ ቀጽሪ ቤተ ክርስቲያንና እንታይ እዩ ዝግበር ዘሎ!? ትርጉምበቤተክርስትያናችን ቅጽር ላይ ምን እየተደረገ (እየሆነ) ነው ያለው?” በሚል ርዕስ በታህሳስ 30 1993 .. ፍኖተ ብርሃን ለንባብ ያበቃችው አንቀጽ እንደሚከተለው ታስነብበናለች። በትግርኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጀ ሙሉ ይዘት ለማብንበብ እዚህ ይጫኑ (1)

ስለ ፍኖተ ብርሃን በእጄ ከሚገኙ ደርቅና ህጋዊ መረጃዎች ለመረዳት እንደተቻለ በአሥመራ የምትገኘውን ብቸኛ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ጋዜጣ መሆንዋን እና በአሁን ሰዓት ጋዜጣዋ በመንግሥት አካላትበማህበረ ቅዱሳንተንኳሽነት ከተዘጋች ስምንት ዓመታት እንዳስቆጠረች ያመላክታሉ። በተመሳስይ ይህ ማኅበር (“ማኅበረ-ቅዱሳን) በአንጋፋው ዜና ቤተ-ክርስትያን የኢ////ያን ብቸኛ ጋዜጣ ያሴረው ሴራና የከፈተበትን የሥም ማጥፋት ዘመቻ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው።

የንባቡ አዘጋጅ የሆኑት ሥማቸው ከአዘጋጁት ጦማር ሥርዘአንበሳ ማርቆስበማለት ያሰፈሩ እኚህ ጸሐፊ እንዲህ በማለት የርዕሳቸውን ሐተታ ይከፍታሉእወ ንዘይትፈልጦ ጉዳይ እንታይነቱ ንኽትፈልጦ ምሕታት ንቡር እዩ። እዚ አብ ቤተ-ክርስቲያና ክምዕብል ዝረአ ዘሎ ሓደገኛ ክስተት ውን እዩ እንታይ ዝዓይነቱ ተልእኾ ንምፍጻም ይጎዓዝ ከምዘሎ ስለ ዘይፈለጥናዮ ክንሐትት ግድነት ኮይኑና ተረኺቡ አሎ። ብርግጽ እውን ዘተሓታትት ጉዳይ እዩ።ትርጉምአዎ የማታውቀውን ጉዳይ ማንነቱን ለማወቅ መጠየቅ ሃጢአት የለውም። ይህ በየአብያተ-ክርስትያናችን ሥር እየሰደደ (እያደገ) እየታየ ያለው አደገኛ ክስተትም ምን ዓይነት ተልዕኮ ለመፈጸም እየተጓዘ እንዳለ ስለማናውቀው መጠየቁ የግድ ሆኖብን ገኝተዋል።በማለት ቀደም ብሎ በደርግ ዘመነ መንግሥት በቀድሞ መጠሪያ ስሙአጠቃላይ ጉባኤተብሎ ስያውክ የነብረና በኤርትራ አብያተ-ክርስቲያናት በእንጭጩ የተቀጨ አሁን ደግሞ 30 ዓመታት ትግል በኃላ የተገኘውን ነጻነት የኤርትራ ህዝብ ሰላሙን እንዳያጣጥም በሃይማኖት ሥም ብቅ ጥልቅ እያለ ወጣቶችን ከአባቶች ካህናት እናቶችንም እንዲሁ ልጆቻቸው የሆኑትን ሰንበት /ቤት ተማሪዎች በለኮሰው እና ብሚጭረው የጸብ እሳት ተከትሎ የሆነውን አስመልክተው የታዘቡትን አንድ በአንድ ያስነብቡናል በማስቀደም ግን ወደ ጽሐፊው የደራሽ ያለህ! የህግ ያለህ! የሚል የአቤቱታ ድምጽ ከመዝለቄ በፊት ፀሐፊው በጽሑፋቸው 2 አንቀጽ ያሰፈሩትን ትንቢታዊ ቃል ላስቀድም እንደሚከተለውም ይነበባልእዚ ስውር ረቂቅ ተንኮል ክህልዎ ይኽእል እዩ ተባሂሉ ዝጥርጠር ዘሎ መግለጺ ዘይርከበሉ ጽላለ ብኃይሊ ሕጊ ክዕገት እንተደአ ዘይተገይሩ አብ ህልውና ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ከቢድ አሉታዊ ጽልዋ ክገድፎ ከምዝኽእል ምግማቱ ዝጽግም አይኮነንትርጉምይህ ስውርና ረቂቅ ተንኮል ሊኖረው ይችላል ተብሎ እየተጠረጠረ ያለው ቃላት የማይገልጸው እብደት በህግ የበላይነት ካልተገታ (እንቅስቃሴው ከወዲሁ እንዲገታ ካልተደረገ) በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ህልውና ከባድ አሉታዊ ተጽእኖ (ጠባሳ) ሊተው እንደሚችል መገመቱ የሚያስቸግር አይሆንም። በማለት ስጋታቸውን በመግለጽ ነበር ወደ ቀጣይ መልዕክታቸው የዘለቁ።  ነጥቦቹን አለፍ አለፍ እያልኩ አቀርባለሁ። (ደመቅ ብለው የሰፈሩ ዓረፍተ ነገሮች ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተመለሱ ሲሆኑ ተጭነው እንዲያነቡ በቀረቦሎትም በመጫን ህጋዊ መረጃውን ማንበብ ይችላሉ።)

እንደ ብርሃን መልዓክ ራሱን እየለዋወጠ ባማሩ ስሞች ተሸፍኖ አውዳሚ አጀንዳውን እውን የሚያደርግ በሀገራችን ምድርማኅበረ ቅዱሳንበመባል የሚታወቀው በአሥመራና አከባቢዎችዋ ደግሞ ከኢትዮ-ኤርትራየደንበርውዝግብ በኃላ ለይቶለት ከኢትዮጵያ ወደ ትውልድ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረጉ ትውልደ ኤርትራውያን አማካኝነት በሰለጠነና በተጠናከረ መልኩታማልዳለችበሚል መደልያ ሥም ተደርጅተው (“ማኅበረ-ቅዱሳንማለት ነው) በኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናትና እንዲሁም ደግሞ በየአጥቢያው የሚገኙትን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሰላማዊና መንፈሳዊ ቅብብል እንዳይኖራቸው ያሴረውን የማፈራረስና የማለያየት፤ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመህ ደግሞ የቤተ-ክርስትያን ሥልጣን መቆናጠጥና ማን ነህ? ባይ በሌለበት ሀበተ ንብረትዋ የመዝረፍና የማውደም ሰይጣናዊ ህልሙ እውን ከማድረጉ በተጨማሪ ክርስቶስ ኢየሱስ በደሙ በመሰረታት ቤተ-ክርስትያን ያደረሱትን ውድመት እዚህ በመጫን ያንብቡ። በትግርኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጀ መቃልሕ ጋዜጣ እዚህ በመጫን ያንብቡ (2) ይህ 7 ዓመት በኃላ 1993 .. በእኚህ ጸሐፊ የተተነበየውን የትንቢት ቃል 2000 . .. በተመሳሳይ ወርና ዕለት ፍጻሜውን ያገኘ የማይዘነጋ አስገራሚና አሳዛኝ ታሪክ ነው።

ይህም ብቻ አይደልም ከዚህም በኃላ 2001 .. በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት ሰንበት /ቤት ያልተለመደና እንግዳ ነገር ተጠናክሮ ሲቀጥል እነዚህኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንጠብቃለን የቅዱሳን የአባቶቻችን ዝክር እንዘክራለን”  የሚሉ በመምሪያ ደርጃ ሳይሳካላቸው ሲቀር በአንዲት አጥቢያ /ያን ባገኙት ቀዳዳ ተጠለው መላ የኤርትራ አብያተ ክርስትያናትን የሚያምሱ ጎበዞች በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት የደረሰውን ጉዳት ኃላፊነቱ ወስደዋል። ምክንያታቸውም ሲገልጹእነዚህ ባለፉት ጊዜያት በሥላሴና ቅድሰት ማርያም ቅጽር ግቢ ውስጥ የሆነውን በነውጥ የታጀቡ አለመግባባቶች እነዚህ በኦርቶዶክስ በሰንበት /ቤቶች ተወሽቀው ሌላ ኃይማኖት እያስፋፉ ያሉ ቡዱኖች ዓላማቸውን ለማክሸፍ ከቤተ-ክርስትያን ለማባረር መሆኑንዲያቆንአኽሊለማርና ሌሎች የማኅበራቸው አባላት ቀስተደበና ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ገልጸዋል ይላልበትግርኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጀ ሙሉ ይዘት ለማብንበብ እዚህ ይጫኑ (3)ዲያቆንአኽሊለማርና ማኅበሩ ማን ናቸው? በክፍል -2 በስፋት ተካተዋል።

ወደ ፍኖተ ብርሃን ጋዜጣ ልመለስለመሆኑ እነዚህ ከመጋራጃ በስተጀርባ ተደብቀው ምንም የማያውቁ ንጹሐን በማነሳሳናት በመቀስቀስ (በውሸት ፕሮኮጋንዳ) አብያተ ክርስትያን እንዲመዘበሩ እያደረጉ ያሉ ሰው መሰል አጋንንት ምንድ ነው የሚፈልጉት? ምናልባት እንደነሱ አባባል በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥም እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች የተዋህዶ (እምነታችን) አይደለም በማለት ነው ሊያሳምኑን የሚፈልጉት። ባይሆን እነዚህ አሁንመናፍቅእየተባሉ እየተከሰሱ ያሉና እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ እየተወገሩ (እየተቀጠቀጡ) ያሉ ሰንበት /ቤቶች በሥጋ ወደሙ ተወስነውና ጸንተው ህይወታቸውን በታማኝነት የሚመሩ የቤተ-ክርስቲያን ልጆች የሚመሩ መሆናቸውን ሊታወቅ ይገባዋል። እነዚህ የወጥቶች ሰንበት /ቤቶች ላለፉት 50 ዓመታት ለተዋህዶ እምነታችን እድገት ያበረከቱት አስተዋጽኦ የታሪክ ማህደሮች አፍ አውጥተው መናገር (መመስከር) እንደሚችሉ ይገነዘቡት (ይረዱት) ይሆን?” (ከትግርኛ የተተረጎመ)

በሁለተኛ መጽሐፌ (“ማኅበረ-ቅዱሳንወይስ ማኅበረ ሰይጣንክፍል 2) ሰፋ ባለ መልኩ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት ማኅበሩ  (“ማኅበረ-ቅዱሳን”) በሀገራችን በኢትዮጵያ በተለይ በአሲኣ አበባ ከተማ ዛሬ ያለበትን የድጥ ከፍታ ይቆም ዘንድ ከተጠቀመባቸው መሰላሎቹ መካከል አንደኛ ቀድሞ የነበሩት ቤተ-ክርስትያኒትዋ ባስቀመጠችው ሥርዓትና ትምህርት ጠብቀው ሐዋርያዊ ተልዕካቸውን ሲያከናውኑ የነበሩትን በህገ ቤተ-ክርስትያን ሥር የሚተዳደሩ ግዴታቸውን በሚገባ የተወጡ ማህበራት ሥም በማጉደፍና መልካም የሆነውን ክርስቲያናዊ አገልግሎታቸው የጥላሸት በመቀባት ነበር ገዳይ ማንነቱ በነጭ ካባ አልብሶ በምእመናን ፊትም ሆነ በቤተ-ክርስትያን መሪዎች ፊት ከኃላ እሳት አንድዶ ሲያበቃ ፊት ለፊት ደግሞ ምላሱን በዘይት ቀብቶ እንደ እባብ እየተቅለሰለሰና እጥፍ ዝርግት እያለ በሸመተው የየዋሃን ልብ የወጣው። የቤተ-ክህነት በር መግቢያ (ገጸ በረከት) ይሆኑልኛል ያላቸውን ሁሉ ደግሞ ፋይል ጠርዞ አያስበሉም ብሎ የፈረጃቸው እንደሆነ በልቶ ነው። በየክፍለ ሀገራቱ አድባራትና ገዳማት የፈሰሰ ደምና የወደቀች ነፍስ ድጋሜ መዘገቡ አንባቢን ማሰላቸት ይሆንብኛል። ምሥክር ባይኖርም የአቤልን ደም የተመለክተ እግዚአብሔር ግን ዛሬም ጻዲቅ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በማኅበሩ የተዘጋጀ የክስ መዝገብ በተከታታይ በጋዜጣና በመጽሐፍ መልክ አትሞ የነገደባቸውን እንዲያነቡ አበረታታለሁ።

የሚደንቀው ይህ ሰይጣናዊ ስትራቴጂው በኢትዮጵያ ምድር ሲሳካለት በተመሳሳይ ወቅት በኤርትራ ምድር ባካሄደው ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻው ግንማኅበረ ቅዱሳንበትልቅ ኪሳራ የተመታበትና ሽንፈት የተከናነበበት አጋጣሚ ነበር። በኢትዮጵያ የብዙዎች ንጽሐን ደም አፍስሶና መልካም ሥማቸውን አጥፍቶ በመምሪያ ደረጃ (ሥር) ቦታ ሲያገኝ በአሥመራ ከተማ ለጊዜውም ቢሆን ህፍረትን ነበር የተከናነበው ለምን? ማኅበሩ (“ማኅበረ ቅዱሳን”) ይበጀኛል ብሎ በዘረጋው ወጥመድም ሆነ ዕቅዱን በሚያስፈጽሙ ጀሌዎቹ የተፈጠረ ክፍተትና ስህተት ሳይሆን ከተገኙ ገለልተኛ መረጃዎች ለመረዳት እንደተቻለ በኤርትራ ምድር የሚገኙትን በየአጥቢያ አብያተ ክርስትያናቱ  የሚገኙት ሰንበት /ቤቶች በሚገባ የተደራጁና የተቋቋሙት ከመሆናቸው የተነሳ ዕቅዱን ከሽፎበታል ለዚህም ነበር ማኅበሩ (“ማኅበረ ቅዱሳን”) በተራ ወሬና አሉባልታ ዘመቻው ሳይሳካለት ሲቀር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ዓይኑን ሳያሻ እንዲህ ዓይነቱ አውዳሚ ጭፍን እርምጃ የወሰደው በኤርትራ ምድር።

ጸሐፊውየጊዜ ጉዳይ ይሆን እንደሆነ እንጂ እነዚህ ለጥፋት የታጠቁ እኩያን ሰዎች የእግዚአብሔር ቤትን የሚያክል ቅዱስ ቦታ (ስፍራ) ደፍረው ከተጠያቂነት ያመልጣሉ የሚል ጥርጣሬ የለንም።በማለት የጻፉትን ቃል ሳስበው የእግዚአብሔር ሥራ ይደንቀኛል ሁለቱ ሉአላዊ ሀገራት የየራሳቸውን መውጫ መግቢያ ከማበጀታቸው በፊት በአንድነትና በህብረት ይወጡና ይገቡ በነበሩበት አንድም ማህበሩ (“ማኅበረ ቅዱሳን”) ከአዲስ አበባ እስከ አስመራ መዋቅሩን ዘርግቶ መሥራቱ በምላሱ የሚጸየፈውን ፖለቲካ ምን ያህል የተነከረ ፍላጎት እንዳለውና በዋናነት ግራ ቀኙን አይቶ ፍላጎቱ የሚያረካበት መንገድ እንደመሰላል ሊጥቀቀምባት ያጫት ቤተ-ክርስትያን ምን ያህል እንደቀለደባትና እየቀለደባትም እንዳለ ነው የሚያመላክተው።

ቤተ-ክርስትያንን ያለ ምስክር የማይተው አምላክ ምንም መንግሥታት ቢለያዩ ጥፋተኛ በጥፋቱ የሚቀጣበት ዘመን ይመጣል በማለት ዛሬን ከአስር ዓመታት በፊት አይተው ይህን የመሰለ መረጃ እጃችን ሊደርስ ችለዋል። በዚህ አጋጣሚ ላሰምርበት የምፈልገው ነጥብ ቢኖር ርኩሳን ሳሉ በቅዱሳን ሥም የተደራጁ ደም የተጠሙ ዛሮች ለጥፋትና ለአመጽ እንቅልፍ አጥተው ድንበር የለሽ ሰይጣናዊ አገልግሎት ለመስጥት ካላፈሩ በደም ዋጋ የተመሰረተችው የክርስቶስ አካል ለመልካም ነገር ለማጀጋጀትማ እዴታ? የአገልግሎት ዓላማም ትውልድን ማዳን ሆኖብን እንጂ የማህበሩ እውነተኛ ማንነትማ መቼ ገለጥነውእና ነው። በውህኒም የሚያስወረውረን በስደት ምድርም የሚያንከራትተን ዛሬም እንደትናንቱ በእውነተኛ ድፍረት ለጊዜው የሚመጥን እውነት የምንሟገተው የያዝን ይዘን እንጂ በአቋራጭ ለመበልጽግ ነው የሚል አስተሳሰብ ሞኝነት አይገልጽልኝም።

በተረፈ መተዳደሪያ ደንቡ፣ ህጉ የሚለው በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ-ክርስትያን የሚከናወን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በሰበካ ጉባኤ ፈቃድና እውቅና እንደሚሰራ ነው የሚታወቀው። እውነቱ ይህ ከሆነ ታድያ በየትኛው ህግ ነው እነዚህ በሃይማኖተኝነት መንፈስ የሰከሩ ግለ ሰቦች (ጨለምተኞች) ለእነዚህ የሰንበት /ቤት ወጣቶች በኑፋቄ ሊከስዋቸው የሚቃጣቸው? ለመሆኑ ለተዋህዶ እምነት ተከታዮች ምእመናን ወክለው ዱላ ሊያነሱና ድንጋይ እንዲወረውሩ እንዲፈነክቱ (እንዲያደሙ) ውክልና የሰጣቸው ከቶ ማን ነው? ውክልናው የሰጣቸው አካል አለ? መጽሐፍ ቅዱስም እንደሆነሰይፍን የሚያነሱ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስበማለት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው (ማቴ. 2652)

እውነት ነው! በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት የሰንበት /ቤቶ ማደራጃ መምሪያማኅበረ-ቅዱሳንንአስመልክቶ ካቀረባቸው መረጃዊ ነጥቦች መካከል አንዱ ይሄ ነበር በሰንበት /ቤት ማደራጃ መምሪያ ሥር የሚተዳደር ሆኖ ሲያበቃ የወደውን በውዳሴ ከንቱ ሲያጅብ የተቃወምውን ሁሉ ደግሞ በርካሽ ቃላቶቹ ሲያንከብልል ነበር የከረመው።

ያም ሆነ ይህ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያናችን ህልዋና ሉአላዊነት የተፈጸመውን ድፍረት የተሞላበት ወንጀል ተድበስብሶ እንዲያልፍ ስለማይገባው በዚህ ጉዳይ ላይ በኃላፊነት የሚጠየቅ ማን ነው? አማኝ ህዝብ ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት እንዳለው ታውቆ የሚመለከታቸው የቤተ-ክርስትያን የበላይ አካላት (መሪዎች) በፍጥነትና በጥራት የማጣራት ሥራ እንዲካሄድ እርምጃ እንዲወስዱ በቅድስት ቤተ-ክርስትያን ሥም እንማጸናለን።በማለት ሊቃውንተ ቤተ-ክርስትያን መምህራን በእነዚህ ተቆርቋሪዎች ነን ባዮች አጥፊዎች በቤ/ያን ላይ የቀሰሩትን ገዳይ ጦርና አይኑ ያወጣ ዝርፍያ አስመልክተው የሚመልከታቸው አካላት አስቾካይ መፍትሔ ያደርጉ ዘንድ ጥያቅያቸውን በምህጽንታ ያቅርባሉ።

ይህን ጽሑፍ በተመለከተ በቀዳሚነት ከምናነሳቸው ጥያቄዎች መካከል፥

1. ይህ ጽሑፍ በማን ላይ ነው የተጻፈ? አድራሻ የሚያደርገው ማንን ነው? ሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያን አክብረን እናስከብራለን የአባቶቻችን ትውፊት ጠብቀን እናስጠብቃለን ከቀድሞ ዘመን ዝንፍ አንልም የተዛነፈ ቁልቁል እንደፋለን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፤ የሐዋርያት፤ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፤ ትሩፋትና አማላጅነት እንዘክራለን በሚሉ ወይስ በአንጻሩ ይህን የሚቃወሙመናፍቃንበሚል ቅጽል ስም በሚታወቁ ግለሰቦችና ማህበራት ላይ የተጻፈ ነው? ብዙም ስሌት ውስጥ ሳንገባ እነዚህ ሁለት ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅብናል።

ልጠይቆት?

ለምሥክርነት አይጠሩም! ቢሆንም እየተሰደደ፣ እየተገፋና  መልካም ስሙና ዝናውን እየጠፋ ያለው ማን ነው? “ማህበረ-ቅዱሳንወይስ ሌላ አለ ብለው ይጠረጥራሉ? “ማኅበረ-ቅዱሳንሲሰደድ ነው ወይስ ሲያሳድድ ነው የሚያውቁት?

ጽድቅና ቅድስና ከእኛ ወድያ ላሳር! ከሚሉትወንድሞችመካከል ጸብና መለያየትን እንደ ስጦታ ማበርከት ይጠበቃል ብለው ያምናሉ? ስጦታዬ ነው በማለት በዚህ አገልግሎት የተጠመደስ ማን ነው? “ማኅበረ ቅዱሳንወይስ አሁንም ሌላ ይኖራል ብለው ይገምታሉ?

ማሳሰቢያ

ማኅበረ ቅዱሳንበግብጽ ምድር ንኡስ ማዕከል ከፍቶ ከመንቀሳቀስ ያልተመለሰ ለረጁም ዘመናት የኢትዮጵያ ግዛት የነበረችውን በባህል በቋንቋ በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወት አንድ የነበረ ህዝብ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለነበረውም እንዲሁም ደግሞ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በተደረጉ ትውልደ ኤርትራውያን አማካኝነት መርዙን አልረጨም ብሎ ማሰብ ሞኝ ያስመስላል። ባህር ተሻግሮ የሊቃውንት አባቶች ስም ከማጥፋትና ከመሳደብ ያልተመለሰ ማኅበር ይህን ለማድረግ አስመራ ይርቀውል ማለት ጠቢብ የሚያሰኝ አይመስለኛም።

ስለወንጌል” “ለወንጌልቆመናል ሲሉ በአሥመራ ከተማ በአጠቃላይ በኤርትራ ግዛት ላይ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አልነበረንም የለንምም ቢሉ ወንጀል ከመሆኑ በላይ ወንጌል ለኤርትራ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልተፈቀደላትም አልተሰጣትም የማለት ያህልም እንደ ሆነ ግምት ውስጥ በማስገባት ጥያቄዎትን ይሰንዝሩ።

እውነትና እርግዝና ተሎ አይወጣም እንዳሉት አበው በክፍል ሁለት ጠንከር ባሉ መረጃዎችና የኢትዮ-ኤርትርየደንብርውዝግብን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲገቡ የተደረጉ ትውልደ ኤርትራውያን  በኢትዮጵያ ምድር በነበራቸው ቆይታበማኅበረ ቅዱሳንሰይጣናዊ አገልግሎት በአባልነትና በአመራር ቦታ ላይ ታቅፈው እሳት ሲያነዱ የነበሩ በርከት ያሉ ግለሰቦች በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ በኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስትያናት የፈጠሩት ውዝግብና መበጣበበጥ አስመልክቶ ከአንድ የነጻ ፕሬስ ውጤት የሆነችው ቀስተ ደበና ጋዜጣ ያካሄዱትን ቃለ ምልልስ ይዤ ሳምንት በድጋሜ እስክንገናኝ የአምላካችን ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።

ቀስተደበና፥ እናንተ ከኢትዮጵያ የተባረራችሁ ናችሁ? ... ሳምንት

የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ሀገራችንና ቤተ-ክርስቲያናችን ይጠብቅ!

ጥበብ በዚህ አለ!

/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Diocese



 



 


ካብ ውሽጢ ኤርትራ ዝተረኽበ ንቤተ ክርስቲያን ተዋህዶ ንምቁጽጻር ብመንግስቲ ኤርትራ ክካየድ ዝጸንሐን ዘሎን ሽርሒ ዘቃልዕ ቪድዮ 



Support Tewahdo TV

Gofundme


Support Diocese

PayPal


ድኳን መጻሕፍቲ/Book Store


ጋዜጣ ፍኖተ ብርሃን፡ ልሣን

 ቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ


ስብከተ ወንጌል


ራድዮ ቃለ ኣዋዲ


መጻሕፍቲ - Books 


ጾምን በዓላትን


Diocese Churches

 

Radio Tewahdo

 Video - Youtube

TV Tewahdo

A Message from H.G. bishop Mekarios

መጸናንዒ ቃል ብብጹእ ኣቡነ መቃርዮስ

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተዋህዶ ብኸመይ

</div